Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከህወሓት ታጣቂዎች የቡድን መሳሪያ ተረከበ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከህወሓት ታጣቂ ሃይሎች የቡድን መሳሪያ ተረከበ፡፡

ርክክቡ በመቀሌ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ ልዩ ቦታው ላጪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተካሄደ ሲሆን፥ በርክክብ መርሐ ግብሩ የአፍሪካ ህብረት ታዛቢዎች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተወካይ ብርጋዴር ጀነራል ደርቤ መኩሪያ እንደገለጹት የመሳሪያ ርክክቡ የሰላም ስምምነቱ አንድ አካል ነው።

በርክክቡም የቡድን መካከለኛ መሳሪያ የሚባሉ የጦር መሳሪያዎችን መረከባቸውን ገልጸዋል።

የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች ተወካይ ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ኃይለ በበኩላቸው የቡድን መሣሪያ ርክክቡ በሰላም ስምምነቱ መሰረት መፈጸሙን ገልጸው፥ ለሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት የበኩላቸውን እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።

ርክክቡን የታዘቡት የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ እና አረካካቢ ኮሚቴ አባል ብርጋዴር ጀነራል ቴፎ ሶኮሌ ርክክቡ የሰላም ስምምነቱ በጥሩ ሁኔታ እየተፈጸመ ለመሆኑ ማሳያ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.