Fana: At a Speed of Life!

ጦርነቱን በመሽሽ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ያሉ ሱዳናውያንን በመልካም ሁኔታ እየተስተናገዱ  ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን ባለው ጦርነት ወደ  ኢትዮጵያ እየመጡ ላሉ ሱዳናውያን የሁለቱን አገር ህዝቦች የቆየ ወንድማዊ ግንኙነት ባገናዘበ ሁኔታ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በዚህም ÷በራሳቸው አቅም ኢትዮጵያ ውስጥ ለመቆየት ወይንም ወደ ሶስተኛ አገር ለመሻገር የሚፈልጉ ሱዳናዊያን እንደማንኛውም  የውጭ ዜጋ የመግቢያ ቪዛ እየወሰዱ በመስተናገድ ላይ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በተጨማሪም ÷ወደ ስደተኛ ካምፕ ለመግባት የሚፈልጉ ካሉ ቪዛ ሳያስፈልጋቸው እየተስተናገዱ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው፡፡

ኢትዮጵያ ሱዳናዊያንን በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ቀርቶ በማንኛው ወቅት በጸጋ ትቀበላልች ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡

ሱዳናውያን ሁለተኛ አገራቸው በሆነችው ኢትዮጵያ የሚያገኙትን አገልግሎት ይበልጥ ምቹ ለማድረግም ከሚመለከታቸው መ/ቤቶች የተውጣጣ ግብረ ሀይል እየሰራ  መሆኑ ተነስቷል፡፡

ከተባበሩት መንግስታት አካላት ጋር በመቀናጀትም የሁለቱን አገራት ህዝቦች የቆየ ወንድማዊ ግንኙነት ባገናዘበ ሁኔታ በመተማ የመግቢያ ኬላ የተቀላጠፈ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.