Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የክብር ቆንስላ በጣሊያን ጄኖአ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣሊያን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የክብር ቆንስላውን በጣሊያን ጄኖአ መክፈቱን አስታውቋል፡፡

በመክፈቻ መርሐ-ግብሩ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ አመራሮች ፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ፣ የጄኖአ ከተማ አስተዳደርና አመራሮች እንዲሁም ባለሐብቶች እና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ እና የክብር ቆንስል ሆነው የተሾሙት አቶ ጃንፔሮ ሱቺ የተመራ የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እንደተሰጠና በሀገሪቷ ባሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ላይም ሰፊ ውይይት እንደተካሄደ ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የጣሊያን የውጭና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አምባሳደር ጂዩሴፔ ሚስትሬታ የክብር እንግዳ ሆነው መገኘታቸውም ተመላክቷል፡፡

በመድረኩ በኢትዮጵያ በሎጂስቲክስና ታዳሽ ኃይል ዘርፍ መዋዕለ-ንዋያቸውን እያፈሰሱ የሚገኙ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ስላለው ሠላም አስተማማኝ እና ሰፊ ገበያ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.