Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ሠላምና ጸጥታ ዙሪያ ለውጥ መመዝገቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሕዝብና የጸጥታ መዋቅሩ በመቀናጀት በሰሩት ስራ በሠላምና ጸጥታ ዙሪያ ለውጥ መመዝገቡን የከተማዋ ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ እና የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ከማዕከል እስከ ቀጠና ከሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማና በወቅታዊ የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡

የከተማው ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ÷ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ወንጀልን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።

ውጤቱ የተገኘው ህብረተሰቡን የሰላምና ደህንነት ባለቤት በማድረግ ተቀናጅቶ መስራት በመቻሉ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡

ከተማ አስተዳደሩ የከተማዋን ሠላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በሁሉም የከተማ አካባቢዎች በርካታ የሰላም ሠራዊት ማደራጀት መቻሉንም አንስተዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በርካታ ሰዎች በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓልም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.