Fana: At a Speed of Life!

“የፒያኖዋ እመቤት” ን የሚዘክር መርሐግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “የፒያኖዋ እመቤት” እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ የሚዘክር መርሐግብር ተካሂዷል፡፡

መርሐግብሩ በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተካሄደ ሲሆን ፥ ለዘርፉ ያደረጉትን አበርክቶ በማስመልከት የኮሌጁ የሙዚቃ ትምህርት ክፍል በስማቸው ተሠይሟል።

በመርሐግብሩ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፣ የቀድሞ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሰብሳቢ አርቲስት ደበበ እሸቱ እንዲሁም አንጋፋና ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የመግቢያ ንግግር ያደረጉት የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ የመርሐግብሩ ዋና ዓላማ ለእማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ መታሰቢያና ምስጋና ማቅረብ ነው ብለዋል።

እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፍ ያሳረፉት አሻራ የገዘፈ መሆኑን ጠቅሰው ፥ ይህም መርሐግብር ስራቸውን ለመዘከር የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።

በስማቸው የተቋቋመው ምግባረ ስናይ ድርጅት ለኮሌጁ የሙዚቃ ትምህርት ክፍል የሙዚቃ መሳሪያዎችን ድጋፍ በማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

የቀድሞ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሰብሳቢ አርቲስት ደበበ እሸቱ ፥ እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ ቁምነገረኛና መካሪ ሰው እንደነበሩ አውስቷል።

የእማሆይ ፅጌማርያም ሥራዎች በወረቀት ላይ ብቻ ሰፍረው የሚነገሩ ሳይሆን በሰዎች አእምሮ ታትሞ የሚቀር ነው ሲልም ነው ያመላከተው።

አክሎም ፥ የእማሆይ ፅጌማርያም የሙዚቃ ቅንብር ክላሲክ የሚባለው የሙዚቃ ዘርፍ ዕንቁ ነው በማለት ገልጿል።

በኢትዮጵያ ቀዳሚዋ የቫዮሊንና ፒያኖ አቀናባሪ የነበሩት እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ ባሳለፍነው መጋቢት ወር ማረፋቸው ይታወሳል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.