Fana: At a Speed of Life!

14ኛው ከተማ አቀፍ የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ 14ኛው ከተማ አቀፍ የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል ሊካሄድ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡

ፌስቲቫሉ “በሥነ ጥበባት ሕብራዊ መልክ የተዋበች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ከግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት ነው በግዮን ሆቴል የሚካሄደው፡፡

ለ14ኛ ጊዜ በሚዘጋጀው ፌስቲቫል ላይ የሥነ ጥበብ እንቅስቃሴዎች፣ የተለያዩ ውድድሮች፣ ዐውደ ርዕይ እና ሥነ-ጥበባዊ ክዋኔዎች እንደሚካሄዱም በቢሮው የኪነጥበብ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሠርፀ ፍሬስብሃት ተናግረዋል።

በከተማዋ ያለውን የኪነ-ጥበብ ሃብቶች በዕይታዊ እና ክውን ጥበብ÷ አጉልቶ ለማሳየት የሚረዳ ዓመታዊ ትልቅ የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል በየዓመቱ በደማቅ ሁኔታ እንደሚዘጋጅ አንስተዋል።

በፌስቲቫሉ የሦስት ቀናት መሠናዶዎችም፣ በዕይታዊ ጥበባት፣ በክውን ጥበባት፣ በሥነ ፅሑፋዊ ጥበባት መስኮች ሥራዎች እንደሚቀርቡ መግለፃቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.