Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ሰላምን ለማረጋገጥ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል መንግስት ሰላምን ለማረጋገጥ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ሃይሉ አዱኛ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ÷ኢትዮጵያ የተለያዩ እምነት ተከታይ ዜጎች ተከባብረው የሚኖሩባት ሀገር መሆኗን አንስተዋል፡፡

የክልሉ መንግስትም በሃይማኖት እኩልነት የሚያምን እና እውቅና የሚሰጥ መሆኑን ነው ሃላፊው የገለጹት፡፡

የሕገ-ወጥ ቤቶች ፈረሳ ሒደት መስጅድ ላይ ያተኮረ አለመሆኑን ጠቁመው ÷በክልሉ 600 በሚሆኑ ከተሞች የህገ ወጥ ቤቶች ፈረሳ ሒደት እንደሚከናወን ተናግረዋል፡፡

ሕግ የማስከበር ስራውም በዋናነት ህገ ወጥነትን በዘላቂነት ለመከላከል ያለመ ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በቀጣይም የክልሉ መንግስት በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ ከሃይማኖትተቋማት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ማረጋገጣቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የሃይማኖት ተቋማት እና የእምነቱ ተከታዮችም እምነትን ተገን አድርገው ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር የሚሞክሩ አካላትን በጋር እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.