Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን ጦር ድርድሩን ማቋረጡ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ጦር ከተፋላሚ ኃይሉ ጋር በጂዳ ሲያደርግ የነበረውን የተኩስ አቁም ድርድር ማቋረጡን የሱዳን ዲፕሎማቲክ ምንጮች ገለጹ።

ጦሩ ግንቦት ሲጠባ ጀምሮ በሳዑዲ አረቢያዋ የወደብ ከተማ ጂዳ ሲያካሂድ እና በተደጋጋሚ ሲጣስ የቆየውን የተኩስ አቁም እና የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽነትን የማሳለጥ ድርድር ለማቋረጥ መወሰኑ ጋብ የማለት ጭላንጭል ያሳየውን ግጭት እንደ አዲስ ያባብሰዋል ተብሎ ተሰግቷል፡፡

በሱዳን ግጭት በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን መፈናቀላቸውን አልጀዚራ የሱዳን የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ አስነብቧል፡፡

ጦሩ የአሁኑን ድርድር በይደር ከማቋረጡ በፊት ሁለት ጊዜ አጫጭር የተኩስ አቁም ሥምምነት ተደርሶ መጣሱ ይታወቃል፡፡

የጦሩ ቃል አቀባይ ለአሶሼትድ ፕሬስ የዜና ወኪል ተናገሩ ተብሎ እንደተዘገበው የአሁኑ ውሳኔ ተፋላሚ ኃይሎች የሰብዓዊ ድጋፍ የተኩስ አቁም ሥምምነቱን በተደጋጋሚ በመጣሳቸውና በዋና ከተማዋ ካርቱም ውስጥ የሚገኙ ሆስፒታሎችን እና ሌሎች የሕዝብ መሠረተ ልማቶችን መያዛቸውን ተከትሎ የተሠጠ ምላሽ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.