Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ ጎበኙ።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾን (ዶ/ር) ጨምሮ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች አውደ ርዕዩን ጎብኝተዋል።

አመራሮቹ ከጉብኝቱ ጎን ለጎንም በሲዳማና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የተዘጋጀውና በሌማት ትሩፋት የተገኙ ውጤቶችን የሚያስቃኝ አውደ ርዕይን በሳይንስ ሙዚየም መርቀው ከፍተዋል።

በሁለቱ ክልሎች የተዘጋጀው አውደ ርዕይ ላይ የዓሳ ፣ ማር፣ አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና ውጤቶች መቅረባቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

”ከቤተ ሙከራ ወደ አዝመራ” በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ ላለፉት ሦስት ሣምንታት በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ነው።

አውደ ርዕዩን የግብርና ሚኒስቴር፣ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢኒስቲትዩት እና ኢትዮ- ቴሌኮም በጋራ አዘጋጅተውታል።

በአውደ ርዕዩ በኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ ያለበትን ደረጃ የሚያሳዩ ምርቶች፣ የግብርና ቴኖክሎጂዎች እና የምርምር ውጤቶች ለጎብኚዎች ከፍት ሆነዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.