Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከ120 በላይ ኢንዱስትሪዎች ዳግም ስራ ጀምረዋል – ቢሮው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ምክንያቶች ስራ አቁመው የነበሩ ከ120 በላይ ኢንዱስትሪዎች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዳግም ወደ ስራ መግባታቸውን የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ገለጸ፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ አህመድ እድሪስ አንዳሉት÷ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በክልሉ ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች መነቃቃት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

ንቅናቄው ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ ምርት እንዳያመርቱ ማነቆ የሆኑባቸው ችግሮች ተለይተው መፈታታቸውን ጠቁመዋል፡፡

በክልሉ ስራ አቁመው የነበሩ ከ120 በላይ ኢንዱስትሪዎች የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ ወዲህ ዳግም ወደ ስራ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡

ዳግም ስራ የጀመሩት ከፍተኛ፣ መካከለኛ እና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች መሆናቸውን ጠቁመው÷በቅንጅት በተሰራው ስራ ከ2 ሺህ በላይ ፕሮጀክቶች ወደ ግንባታ እንዲገቡ መደረጉንም አንስተዋል፡፡

ንቅናቄው በክልሉ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ጨምሯል ያሉት ሃላፊው÷በዚህም 41 በመቶ የነበረው አማካኝ የማምረት አቅም ወደ 51 በመቶ ከፍ ማለቱን ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.