Fana: At a Speed of Life!

ሲካሄድ የቆየው የግብርና እና ሳይንስ አውደ-ርዕይ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ከቤተ ሙከራ ወደ አዝመራ” በሚል መሪ ሀሳብ ከሚያዚያ 29  ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወርሲካሄድ የቆየው የግብርና እና ሳይንስ አውደ ርዕይ በስኬት መጠናቀቁን የግብርና ሚኒስትሩ  ግርማ አመንቴ(ዶ/ር)  ተናገሩ፡፡

አውደ-ርዕዩ የግብርና ዘርፉን ስኬታማነት ማጠናከር የሚያስችል ውጤት የተገኘበት እና ግቦቹን የመታ  ሆኖ መጠናቀቁንም ሚኒስትሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።

ለአንድ ወር በቆየው በዚህ አውደ ርዕይ ከ88ሺህ በላይ ጎብኚዎች ተሳትፈውበታል ያሉት  ሚኒስትሩ በዚህም በቀን በአማካኝ ከ3 ሺህ በላይ ጎብኚዎች ሲታደሙበት እንደቆየም ተናግረዋል።

በተለይም የግብርናው ዘርፍ የደረሰበት ደረጃ የተመላከተባቸው ፣ ዘርፉን ማሳደግና የተገኙ ስኬቶችን ማጠናከር የሚያስችሉ 4 አውደ ጥናቶች መካሄዳቸውን ሚኒስትሩ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሌሎች ግብርናውን አጋዥ የሆኑ ዘርፎችን ያካተተ አውደ ርዕይ በቋሚነት እንዲካሄድ ጥያቄዎች መነሳታቸውንም ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.