Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስዊድን ስቶክሆልም ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች አሸንፈዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስዊድን ስቶክሆልም ማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ በበላይነት አጠናቀዋል።

በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ ሀገራት የአትሌቲክስ ውድድሮች ተካሂደዋል።

በሳምንቱ ከተደረጉ ውድድሮች መካከል በስዊድን የተካሄደው የስቶኮልም ማራቶን ይገኝበታል።

በወንዶች አትሌት አሸናፊ ሞገስ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ÷ አትሌት ደራራ ሁሪሳ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ጸጋዬ መኮንን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን በበላይነት ጨርሰዋል።

በሴቶች ደግሞ አትሌት ሲፋን መላኩ አንደኛ በመውጣት ስታሸንፍ÷ አትሌት ሶሮሜ ነጋሽ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት የኔነሽ ዲንቄሳ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በስፔን አልባሴቴ የግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች አትሌት ካሳነሽ ባዜ አሸናፊ ሆናለች።

በደቡብ አፍሪካ በተደረገው የኔልሰን ማንዴላ ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት በቀለች ወሬዮ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ማጠናቀቋን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አትሌት ሰላም ገብሬና አትሌት ትዕግስት አያሌው በቅደም ተከተል አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃን ይዘው ውድድሩን ጨርሰዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.