Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዩ ኤን ሃቢታት ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ በሚገኘው ሁለተኛው የዩ ኤን ሃቢታት ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

“ለተሻለ የከተማ ዕድገት!” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ የሚገኘውን ጉባኤ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በይፋ ከፍተዋል፡፡

በከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፈንታ ደጀን የሚመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በጉባኤው እየተሳፈ ሲሆን÷ አቶ ፈንታ ደጀን በመድረኩ ኢትዮጵያን የተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በንግግራቸው÷ የኢትዮጵያ መንግስት በከተማ ሴክተር እያከናወናቸው ያሉ ዋና ዋና የፖሊሲ መዋቅራዊ ለውጦችን ገልጸዋል።

አዲሱ የከተማ አጀንዳ እና የልማት ግቦችን በከተሞች ዘርፍ በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግም የኢትዮጵያ መንግስት ከዩ ኤን ሃቢታት ጋር ያለውን ትብብር እና አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ተናግረዋል።

ጉባኤው እስከ ሰኔ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚቀጥል ከከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.