Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እስከ 2018 ዓ.ም. ድረስ 50 ቢሊየን ችግኞችን ትተክላለች – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እስከ 2018 ዓ.ም. ድረስ 50 ቢሊየን ችግኞችን እንደምትተክል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።

 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ 25 ቢሊየን ችግኞች የተተከሉበት የመጀመሪያው ምዕራፍ መሳካቱን አስታውቀዋል።

 

በሁለተኛው ምዕራፍ ተጨማሪ 25 ቢሊየን ችግኞች እንደሚተከሉ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ አረንጓዴ አሻራ ለትውልድ የሚተላለፍ ቅርስ መሆኑን ገልጸዋል።

 

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር “የአየር ንብረት ለውጥንና የአካባቢ መራቆትን ለመቋቋም የወጠነው ሀገር በቀል አካሄዳችን ነው” ብለዋል።

 

በተጨማሪም “የስራ እድል ለመፍጠር አንዱ መንገዳችን ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ “ለምግብ የሚውሉ ዕፅዋትን በመትከል የምግብ ዋስትናችንን የምናረጋግጥበት አንዱ መንገድ ነው” ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.