Fana: At a Speed of Life!

የዓለም አቀፍ ተፈናቃዮች ቁጥር 110 ሚሊየን ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በግጭት ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 110 ሚሊየን ከፍ ማለቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፍልሰተኞች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ቁጥሩ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ ከተመዘገበው ከ19 ሚሊየን ወደ 108 ነጥብ 4 ሚሊየን ማደጉን የኤጀንሲውን ሪፖርት ጠቅሶ ኤዢያ ዋን ዘግቧል፡፡

የፍልሰተኞች አሃዙ እስካሁን ከተመዘገበው ዓመታዊ የዓለምአቀፍ ተፈናቃዮች ቁጥር አንጻር ከፍተኛው ነው ተብሏል፡፡

በዩክሬን እና በሱዳን የተቀሰቀሱ ግጭቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ማድረጉም ተጠቁሟል፡፡

ቁጥሩ በዚህ ደረጃ ከፍ ለማለቱ ለሥምንት ሣምንታት የዘለቀው የሱዳን ግጭት ዋና ምክንያት መሆኑን የድርጅቱ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.