Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የነጋዴ ሴቶች ኤክስፖ በመዲናዋ ተከፈተ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የነጋዴ ሴቶች ኤክስፖ በአዲስ አበባ ተከፈተ፡፡

ኤክስፖውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በስካይ ላይት ሆቴል በይፋ የከፈቱ ሲሆን፥ በአምራች ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎ ለማረጋገጥ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

ሴቶችን ለሥራ ፈጠራ የሚያነሳሱ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መቀረጻቸውንም አንስተዋል፡፡

ኤክስፖውም የዚሁ አንድ አካል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በኤክስፖው በተለያዩ ርዕሠ-ጉዳዮች ላይ የሚካሄዱ ውይይቶች፣ የባለድርሻ አካላት ምክክር እንዲሁም ሴቶችን የሚያበቁ ሥልጠናዎች ይካሄዳሉ ተብሏል።

መርሐ-ግብሩ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ይካሄዳል፡፡

ሴት ሥራ ፈጣሪዎች ፣ አምራቾችና የንግድ ተቋማትም የተለያዩ ምርቶቻቸውንና አገልግሎታቸውን አቅርበዋል።

ኤክስፖውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ማዘጋጀታቸው ተመልክቷል፡

በሳሙኤል ወርቃየሁ እና መሳፍንት እያዩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.