Fana: At a Speed of Life!

ምዕራባውያኑ ሩሲያ ላይ የጣሉት ማዕቀብ ከውጤታማነቱ ይልቅ ጎድቷቸዋል – አሜሪካዊ የፖለቲካ ተንታኝ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ እና አጋሮቿ ምዕራባውያን ሀገራት ሩሲያ ላይ የተጣሉት ማዕቀቦች ፍሬ አፍርተው ሞስኮ ላይ ጫና እንዳላሳረፉ ዳግላስ አንድሪው ሊትልተን የተባሉ አሜሪካዊ የፖለቲካ ተንታኝ ገለጹ፡፡

“ማዕቀቦቹ እንዳውም ሩሲያን በኢኮኖሚ ከማንኮታኮት ይልቅ ምዕራባውያኑ እና አሜሪካ ላይ መልሰው ጫና አሳርፈዋል” ብለዋል፡፡

አሜሪካዊው ተንታኝ በሴንት ፒተርስበርግ የምጣኔ ሐብት ጉባዔ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ለአር ቲ በሰጡት አስተያየት ነው ይህን ያሉት።

ዳግላስ አክለውም የአሜሪካ መንግስት በሞስኮ ላይ የወሰደው ማዕቀብ የመጣል እርምጃ ዓላማው ግልፅ አይደለም በሚል ቅር መሠኘታቸውንም ገልጸዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ የተጀመረው ዓለም አቀፉ የሴንት ፒተርስበርግ የምጣኔ ሐብት ጉባዔ ላይ ከ130 ሀገራት የተውጣጡ ከ17 ሺህ ላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ጉባዔው አራት ቀናት እንደሚቆይ እና በሩሲያ እና በዓለም ምጣኔ ሐብታዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.