Fana: At a Speed of Life!

“ከዚህ በኋላ ዘረኝነት ያለበት እግርኳስ ውድድር አይኖርም” –  ፊፋ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) ከዚህ በኋላ ዘረኝነት ያለበት እግርኳስ ውድድር እንደማይኖር ገለጸ፡፡

በብራዚላዊው አጥቂ ቪኒሺየስ ጁኒየር የሚመራ ከተጫዋቾች የተውጣጣ የፀረ- ዘረኝነት ኮሚቴ ማቋቋሙን ፊፋ ይፋ አድርጓል፡፡

የፊፋው ፕሬዚዳንት ጂያንኒ ኢንፋንቲኖ ከዚህ በኋላ ዘረኝነት ያለበት እግርኳስ ውድድር እደማይኖር ጠቅሰው÷ “የዘረኝነት ጥቃት በሚከሰትበት ጊዜ እግር ኳስ ጨዋታው ሙሉ በሙሉ መቋረጥ አለበት” ብለዋል፡፡

የፀረ- ዘረኝነት ኮሚቴው በእግር ኳስ የሚሰነዘሩ የዘረኝነት ጥቃቶችን በሕጋዊ መንገድ ለመከላከል እንደሚያግዝም ገልጸዋል፡፡

ዘረኝነት በፊፋ ሕጎች ብቻ ሊቆም እንደማይችል በመጥቀስም የዓለም መንግሥታት እና መገናኛ ብዙኃን የዘረኝነትን አሉታዊ ተፅዕኖ በመግታት ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

ቪኒሺየስ ጁኒየር በቅርቡ ክለቡ ሪያል ማድሪድ ከቫሌንሲያ ጋር ባደረገው ጨዋታ ከደጋፊዎቹ የዘረኝነት ጥቃት እንደተሰነዘረበት አስታውሶ ሜይል ስፖርት ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.