Fana: At a Speed of Life!

አቶ ርስቱ ይርዳ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ሂደትን ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ ላይ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳን ጨምሮ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊና የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ አባል ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ስዩም መኮንን፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ/ር) እና ሌሎች የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር እየተገነባ የሚገኘው አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ የማጠናቀቂያ ሥራ እየተፋጠነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ግንባታው ሲጠናቀቅ በነባሩ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ላይ የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ ይቀርፋል መባሉን በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የግንባታው ተቋራጭ የቻይናው ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ (CCCC) ግንባታውን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ድልድዩ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሏል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.