Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ አፍሪካ 30 ሚሊየን ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) 5 አባል ሀገራት ውስጥ የሚገኙ 30 ሚሊየን ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ሪፖርቶች አመላከቱ፡፡

የተቀናጀ የምግብ ዋስትና ደረጃ ምደባ ተቋም (አይ ፒ ሲ) ሪፖርትን ጠቅሶ ዳውን ቱ አርዝ ጋዜጣ እንደዘገባው ÷ በ7 የኢጋድ አባል ሀገራት ውስጥ የሚገኙ 55 ሚሊየን ዜጎች ለረሃብ አዳጋ ተጋልጠዋል፡፡

በአባል ሀገራቱ የሚገኙ 30 ሚሊየን ዜጎች ደግሞ በዚህ ዓመት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ነው በሪፖርቱ የተመላከተው፡፡

በኢጋድ አባል ሀገራት ለከፋ የምግብ ዋስትና እጦት የሚጋለጡ ዜጎች ቁጥር በየዓመቱ በፍጥነት መጨመሩን የጠቆመው ሪፖርቱ÷ ከፈረንጆቹ 2020 ጀምሮ በየዓመቱ 10 ሚሊየን ዜጎች ለረሃብ ይጋለጣሉ ብሏል፡፡

በሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ያለው የረሃብ ተጋላጭነት ከቀጠናው ሀገራት እጅግ አስከፊ የተባለ ሲሆን÷ ከሁለቱ ሀገራት ብቻ 8 ነጥብ 7 ሚሊየን ዜጎች ለረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ኡጋንዳ ደግሞ የረሃብ ተጋላጭ ዜጎች ያሉባቸው ሌሎች ሀገራት በመሆን የተቀመጡ ሀገራት ናቸው፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ ግጭት በቀጠናው ለምግብ ዋስትና እጦት ተጋላጭነት ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው መባሉንም  የዳውን ቱ  አርዝ መጽሄት ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.