Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና እንግሊዝ በንግድና ኢንቨስትመት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ በንግድና ኢንቨስትመት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ እና የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የንግድ ሚኒስትር ኒገል ሃድልስተን በንግድና ኢንቨስትመንት ዙሪያ አብሮ ለመስራት የሚስችለውን ስምምነት ፈርመውታል፡፡

በዚሁ ወቅት አቶ ገብረመስቀል ጫላ÷ ስምምነቱ በዋናነት ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እያደረገች ያለውን ሁሉን አቀፍ ዝግጅት በፋይናንስና በቴክኒክ ለማገዝ የሚረዳ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ እስካሁን የዓለም አቀፉ የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ረጅም ጉዞ መጓዟን ጠቅሰው÷ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንትን በማሳደግ ተወዳዳሪ ሆኖ መገኝት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የንግድ ሚኒስትር ኒገል ሃድልስተን በበኩላቸው÷ ከኢትዮጵያ ጋር ረጅም አመታትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም የንግድ ድርጅት ውስጥ ያላትን ተሳትፎ እንድታሳድግ በእንግሊዝ በኩል ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነን ማለታቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው ይበልጥ ተጠቃሚ እድትሆን ለማድረግና የንግድ ሚዛኑን ለማሻሻል በሚቻልበቻው ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በጋራ ለመስራትና ለመደገፍ ሀገራቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግም አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.