Fana: At a Speed of Life!

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለብሄራዊ ቡድን 200 ጊዜ በመሰለፍ የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ሰፈረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን 200 ጊዜ ተሰልፎ በመጫዎት ስሙ በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ሰፍሯል፡፡

ሮናልዶ ትላንት ምሽት በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ሀገሩ ፖርቹጋል አይስላንድን በገጠመችበት ጨዋታ 200ኛ ጨዋታውን ለብሄራዊ ቡድኑ አድርጓል፡፡

በጨዋታውም ግብ አስቆጠሮ ሀገሩን አሸናፊ ማድረግ መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡

ይህን ተከትሎም ሮናልዶ በወንዶች ምድብ ለብሄራዊ ቡድን ብዙ ጊዜ የተሰለፈ ተጫዋች በመሆን  የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ሰርተፍኬትን ከጨዋታው በኋላ ተቀብሏል፡፡

ሮኖልዶ ሰርተፍኬቱን ከተቀበለ በኋላ “እዚህ እደርሳለሁ ብየ አላስብኩም፣ይህ ለኔ ትልቅ ክብር ነው፣አዳዲስ ታሪኮችን ማስመዝገቤን እቀጥላለሁ” ብሏል፡፡

ቀደም ሲል ክብረ ወሰኑ በኩዌቱ አጥቂ ባድር አል ሙታዋ ተይዞ የነበረ ሲሆን÷ ሙታዋ ለኩዌት ብሄራዊ ቡድን 196 ጊዜ ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡

የ38 ዓመቱ አጥቂ ክርስቲያኖ የፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሲሆን÷ 200 ጊዜ ተሰልፎ 123 ግቦችን እንዳስቆጠረ ሜይል ስፖርት ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.