Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሕጻናት ክሊኒክ እና የሕፃናት ማቆያ ማዕከልን መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩ በክበበ ፀሃይ ያስገነባውን የሕጻናት ክሊኒክ እና በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነባውን የሕጻናት ማቆያ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች ሕጻናት ከጽንስ ጀምሮ ተገቢውን እንክብካቤ አግኝተው በአካልና አዕምሮ በልፅገው እንዲያድጉ የከተማ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የእናቶችን የኑሮ ጫና ማቅለል የሚያስችል የሕጻናት ማቆያ እና የሕፃናቱን ጤንነት ለመከታተል የከተማ አስተዳደሩ የሕፃናት ክሊኒክ መገንባቱንም አንስተዋል፡፡

በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት 1 ሺህ ተጨማሪ የሕፃናት ማቆያ ማዕከላት እንደሚገነቡ ከንቲባ አዳነች ጠቁመዋል፡፡

በሕጻናት አስተዳደግ ዙሪያ የቤት ለቤት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ የሚሰሩ 1 ሺህ 400 ባለሙያውዎች በዛሬው ዕለት መመረቃቸውንም የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.