Fana: At a Speed of Life!

የክልሉ አመራሮች የተግባር አንድነትን በመፍጠር ውጤት ለማምጣት በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል – አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል አመራሮች የአመለካከትና የተግባር አንድነትን በመፍጠር በሁሉም ዘርፍ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ አሳሰቡ።

በክልሉ የፖለቲካና የጸጥታ ሁኔታና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ የክልል ማዕከል አመራሮች በጋምቤላ ከተማ እየተወያዩ ነው።

በውይይቱ አቶ ኡሞድ ኡጁሉና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ቴንኩዌይ ጆክ እንዲሁም በብልጽግና ፓርቲ የጋምቤላ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ላክዴር ላክባክ ተገኝተዋል፡፡

አቶ ኡሞድ ኡጁሉ÷መድረኩ እንደ ሀገር የተገኙትን ስኬቶችና ጥንካሬዎች በማስፋት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው ብለዋል።

በክልሉ የሕዝቡን ሰላም፣ አንድነትና አብሮነት ይበልጥ በማጠናከር የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ ሁሉም ዜጋ መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል።

አቶ ቴንኩዌይ ጆክ በበኩላቸው÷የክልሉ ነዋሪ የባህል፣ የሃይማኖትና የቋንቋ ልዩነት ሳይገድበው በመከባበርና በአብሮነት የመኖር ባህሉ ክልሉን ሰላማዊ እንዳደረገው ጠቁመዋል።

የክልሉ አመራሮች አንድነታቸውን በማጠናከር የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ፍላጎት ለማሟላት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ መገለጹንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.