Fana: At a Speed of Life!

የ60 ሺህ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ቅድመ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስት እና የግል አጋርነት መርሐ ግብር የ60 ሺህ መኖሪያ ቤቶች ቅድመ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት አካሄደ፡፡

ቤቶቹ በ3 ዓመታት ውስጥ ተገንብተው ይጠናቀቃሉ መባሉን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ከ200 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የአዲስ አበባ ወጣቶች ቀጥተኛ የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩም ተጠቁሟል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ መኖሪያ ቤት የሕዝቡ ቀዳሚ ጥያቄ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በዚህም በመንግስትና በግል ተቋማት ትብብር መስራት የሚያስችል የፖሊሲ አቅጣጫ እና የአሰራር መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱን አረጋግጠዋል፡፡

በመኖሪያ ቤት ግንባታ ለመሰማራት ፍላጎት ካሳዩ 70 የግል ድርጅቶች መካከል ኦቪድ ግሩፕ ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

በቅድመ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ በመኖሪያ ቤቶቹ ግንባታ ዙሪያ እና ባከናወናቸው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ለአስተዳደሩና ለባለድርሻ አካላት ማብራሪያ መስጠቱም ተጠቅሷል፡፡

በዚሁ መሠረት 60 ሺህ ቤቶችን በ3 ዓመታት ውስጥ ገንብቶ ለተጠቃሚዎች ያስተላልፋል ተብሏል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.