Fana: At a Speed of Life!

የ9 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር የአካባቢ ጥበቃ ፕሮጀክት ድጋፍ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በሚቀጥሉት አምስት አመታት ለሚተገበረው የተቀናጀ የአካባቢ ጥበቃና ልማት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል የ9 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ተፈርሟል፡፡

ፕሮጀክቱ የአየር ንብረት አካታች ተቋማዊ የአቅም ግንባታ ፣ ከአየር ንብረት ጋር የሚጣጣም ቴክኖሎጂ ተደራሽነት፣ የተቀናጀ የመሬት አያያዝ እና የገቢ ምንጭ አማራጮችን የማስፋት ክፍሎች ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተመረጡ ክልሎችና ወረዳዎች ተግባራዊ የሚደረግ ነው መባሉን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ ከተመደበው ገንዘብ ውስጥ 8 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር የሚሆነው ‘ግሎባል ኢንቫይሮመንት ፋሲሊቲ’ ከሚባል ዓለም አቀፍ ተቋም የሚገኝ ሲሆን 400 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ደግሞ በተባባሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም እንደሚሸፈን ታውቋል፡፡

የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው፣ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ጌታሁን ጋረደው (ዶ/ር) እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ ቱርሃን ሳልህ ፈርመውታል፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.