Fana: At a Speed of Life!

የቱርክ ባለሃብቶችን በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ለማሳተፍ እየተሰራ ነው – የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርክ ባለሃብቶች በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ እንዲሳተፉ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሀመድ የቱርክ አፍሪካ ቢዝነስ አሶሴሽን ዳሬክተር ፈቲህ አካቡሉትን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የቱርክ የአፍሪካ ቢዝነስ አሶሴሽን ዳይሬክተር ፈቲህ አካቡሉትን ÷ የአፍሪካ መዲናና የበርካታ ዲፕሎማት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካና የቱርክ ባለሀብቶች የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉና ባለሀብቶቹ ወደ ኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ እንዲሰማሩ ለማስቻል በኢትዮጵያ ቢሮ በመክፈት በቅርብ ወደ ስራ እንደሚገቡም ገልጸዋል፡፡

የእርስ በርስ ግንኙነቱን በመልካም መሰረት ላይ ለመገንባት፣ የገበያ ትስስር ለመፍጠርና የቴክኖሎጂና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የሚያስችል ዓውደ ርዕይ በቱርክ ኢስታንቡል እንደሚካሄድም ነው የተነሳው፡፡

ከ1 ሺህ 500 በላይ አምራቾችና ሸማቾች በሚሳተፉበት በዚህ ኤግዚቪሽንና ባዛር የአፍሪካ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲሳተፉ ለማድረግ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የማስተባበር ስራውን እንደሚሰራ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.