Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዓለም ባንክ እና አይ ኤም ኤፍ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአዲሱ የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ “ከአዲሱ የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረናል” ብለዋል፡፡

ባንኩ ለአየር ንብረት ለውጥ፣ ወረርሽኝ፣ ግጭት እና ለመሳሰሉ አዳዲስ ተግዳሮቶች ምላሽ የመስጠት ተልዕኮውን እንዲያጎለብት ኢትዮጵያ እንደምታበረታታ አረጋግጠዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  እና አጃይ ባንጋ በፈረንሳይ ፓሪስ እየተካሄደ ካለው  አዲስ የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ስምምነት ጉባዔ  ጎን ለጎን ነው የተወያዩት፡፡

በተመሳሳይ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ኃላፊ ክሪስታሊና ጆርጄቫ ጋር መወያየታቸውን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ለአየር ንብረት ችግሮች ምላሽ ለመስጠት ድርጅቱ የሚያደርገው የተጠናከረ ጥረትና ቀጣይ ድጋፎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
.

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.