Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ ለሩሲያ እና ዩክሬን ያቀረበችውን የሠላም ዕቅድ ቻይና እንደምትደግፍ አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ ሩሲያና ዩክሬንን ለማሸማገል የምታደርገውን ጥረት ቻይና እንደምትደግፍ አስታወቀች፡፡

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ ÷ የአፍሪካ መሪዎች የሠላም ተልዕኮ አንግበው ሩሲያና ዩክሬንን ለማሸማገል እያደረጉ ላሉት ጥረት አመሥግነዋል፡፡

የሁለቱን ወገኖች ግጭት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶችን ሁሉ ቻይና ትግፋለችም ነው ያሉት።

ድርድር እና ውይይት ከቀውሱ መውጫ ብቸኛ መንገዶች እንደሆኑ መጠቆማቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡

በሌላ በኩል በቻይና የሶቾው ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ቪክቶር ጋኦ ÷ አሜሪካ በሁለቱ ሀገራት ጉዳይ እጇን ማስገባት እስካላቆመች ድረስ ሠላም ማስፈን እጅግ በጣም ከባድ ነው ብለዋል።

አሜሪካ ጦርነቱ በማራዘም በሩሲያ ላይ የጂኦ ፖለቲካዊ ጥቅሟን ማሳካት እንደምትፈልግም ነው የተናገሩት፡፡

በመሆኑም አሉ ፕሮፌሰሩ ÷ ሩሲያና ዩክሬን ከአፍሪካ መሪዎች የሚቀርብላቸውን የሠላም ጥሪ ቢቀበሉ ይበጃቸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.