Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ብሄራዊ አስተግባሪ ኮሚቴ በይፋ ስራውን ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ የፌዴራል ተቋማት ከተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች የተዋቀረው የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ብሄራዊ አስተግባሪ ኮሚቴ ዛሬ በይፋ ስራውን ጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና የእቃዎችና የአገልግሎት ‘ንግድ ኦፈር’ በቅርቡ ለማክሮ ኮሚቴ ቀርቦ መፅደቁ ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎም በ2016 ዓ.ም የሚኖረውን ንግድ ለመጀመር የሚያስችል ስራ ለማቀላጠፍ የሚያስችል እቅድ ላይ ፍሬያማ ውይይት መካሄዱ ተመላክቷል፡፡
በምክክር መድረኩም ስራውን ለማስጀመር የሚያስችል ንዑሳን ኮሚቴዎች እንዲደራጁ ስምምነት ላይ መደረሱንየንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው

አስፍረዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.