Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አባባ የቤት ኪራይ የተጨመረባቸው ነዋሪዎች ቅሬታ የሚያቀርቡበት አሰራር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር የቤት ኪራይ የተጨመረባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን የሚያቀርቡበት አሰራር ይፋ ተደርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ማንኛውም አከራይ እስከ ተወሰነው ጊዜ ድረስ የቤት ኪራይ መጨመር እንደማይችል መወሰኑ ይታወሳል::

በዚህ መሰረትም የቤት ኪራይ የተጨመረባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ማስረጃዎቻቸውን በመያዝ ከፊታችን ማክሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

ነዋሪዎች ቅሬታቸውን በሚኖሩበት ወረዳ የመልካም አስተዳደርና አቤቱታ ስራ ክፍል እንዲሁም የወረዳ ስራ አስፈፃሚ ቢሮዎች በመገኘት ማቅረብ እንደሚችሉ መገለጹንም የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.