Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ እርዳታ ያቋረጡ ድርጅቶች ለማቋረጣቸው ምክንያት ያሏቸውን ጉዳዮች የሚያጣራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ ገብቷል – መንግስት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩ ኤስ ኤይድ እና የአለም የምግብ ፕሮግራም ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ ለጊዜው ለማቋረጣቸው ምክንያት ነው ያሏቸውን ጉዳዮች የሚያጣራ የቴክኒክ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱ ተገለፀ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሸን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ የአለም የምግብ ፕሮግራም እና የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ ለጊዜው ማቆማቸውን አስታውሰዋል፡፡

ይህን ተከትሎ መንግስት ከእነዚህ አካላት ጋር በመሆን የአሰራር ክፍተት አለባቸው የተባሉት ላይ ማሻሻዎችን ለማድረግ እና ህገ ወጥ ተግባር ተፈፅመውም ከሆነ ማጣራቶችን በማድረግ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑን ማሳወቁንም እንዲሁ አንስተዋል፡፡

በዚህም በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መሪነት ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ባለድርሻ ተቋማት ተወካዮችን ያካተተ እንዲሁም ከእነዚሁ ከሰብአዊ ድጋፍ አጋሮች የተውጣጡ አባላት የተካተቱበት የቴክኒክ ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራ መጀመሩን ገልፀዋል፡፡

ኮሚቴው የተለያዩ የመፍትሄ ሃሳቦችን እያቀረበ የአሰራር ማሻሻያ ያስፈልጋቸዋል ያላቸውን ዘርፎችን በመለየት የመፍትሄ ሃሳቦችን እያቀረበ ውጤታማ ውይይቶችን እያደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

የተቋቋመው የጋራ ቴክኒካል ኮሚቴም በዋናነት በአስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ፣ በሴፍቲኔት መርኃ ግብር እና በስደተኞች የሰብአዊ ድጋፍና አቅርቦት እና ስርጭት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

በዚህም እስካሁን መልካም ውጤት መገኘቱን ነው የተናገሩት።

አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ተገቢው ድጋፍ እንዲደርሳቸው በመንግስት በኩል ከተለያዩ አካላት ጋር በትኩረት ሲሰራበት የነበረ ተግባር መሆኑን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ በዚህም ሂደት ውስጥ የህግ የበላይነት መከበር አለበት ብለዋል፡፡

ይህንንም ለማስፈን በተለይ ህገወጥ ድርጊት ላይ የተሳተፉትን ለህግ ሲያቀርብ እና ሰፊ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱንም ተናግረው አሁንም እንደሚቀጥል እና ኮሚቴውም ይህን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

በቅርቡም ኮሚቴው የደረሰበትን ውጤት በይፋ እናሳውቃለን ነው ያሉት፡፡

በፌቨን ቢሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.