Fana: At a Speed of Life!

በተለያየ ሙያ የሰለጠኑ የባሕር ኃይል አባላት ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን የባሕር ኃይል አባላትን አስመረቀ፡፡

ተመራቂዎቹ  በናቪጌሽን፣ ኤሌክትሪሲቲ፣ በኮሙኒኬሽን፣ በአርማመንትና በሌሎች መሰል ሙያዎች በሀገር ውስጥና በውጭ የሰለጠኑ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ÷ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ ሪር አድሚራል ክንዱ ገዙ፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች፣  የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጠንካራና ብቃት ያለው በየትኛውም የውኃ አካል ላይ ግዳጅን መወጣት የሚችል እንዲሁም የመከላከያ ኃይል ላይ ተጨማሪ የማድረግ አቅምን የሚፈጥር ተቋም የመሆን ራዕይ ይዞ እየሠራ መሆኑ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ከምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ቀደም ብለው ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የአየር ኃይል አቪዬሽን ከባድ ጥገና ማዕከል ወደ አገልግሎት የመለሳቸውን ፈጣን ተዋጊ ጀልባዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ተዋጊ ጀልባዎቹ በቀድሞ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አገልግሎት የሠጡ መሆናቸው እና ዳግም የባሕር ኃይሉን ዝግጁነት እንደሚያጠናክሩ ተገልጿል።

የአየር ኃይል አቪዬሽን ከባድ ጥገና ማዕከል ከ30 አመት በላይ ተገለው እና አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ጀልባዎችን ዘመኑ የሚጠይቀውን የፈጣን ተዋጊ ጀልባ ቴክኖሎጂ እና መሳሪያዎች በመግጠም ለግዳጅ ዝግጁ ማድረግ መቻሉን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.