Fana: At a Speed of Life!

የአረፋ በዓልን ምክንት በማድረግ ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 444ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ)በዓልን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ስታዲዮም የሚካሄደው ሃይማኖታዊ ስነ-ስርአት ተጀምሮ እሰከሚጠናቀቀ የትራፊክ መጨናነቅ እንደይፈጠር ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዓሉ በሠላም እንዲከበር የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን ለማክበር ወደ አዲስ አበባ ስታዲዮም ሲመጡ ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ መኖሩን ተረድተው እንደወትሮው ሁሉ ትብብር እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡

በዓሉን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ስታዲዩምና በዙሪያው የሚከናወነው ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓት ተጀምሮ እሰከሚጠናቀቀ ከፒያሳ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ዋናው መንገድ ቴድሮስ አደባባይ፣ ከጎተራ ፣ አጎና ሲኒማ ፣ ሪቼ የሚወስደው መንገድ ለከባድ ተሽከርካሪዎች አጎና ሲኒማ እንዲሁም ለአነስተኛ ተሽከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ወይም የቀድሞ 4ኛ ክፍለ ጦር ጋር፣ከኬኬር ህንፃ ጀርባ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ የድሮ ለገሃር ግምሩክ ዝግ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ፣ በፖሊስ ሆስፒታል ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ አል ሳም ጨለቅለቅ በስርና በላይ መንገድ፣ ከጎማ ቁጠባ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ ፣ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ መብራት፣ ከሜትሮሎጂ በጥቁር አንበሳ ወደ ፖስታ ቤት የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መ/ቤት፣ ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ኦርማ ጋራዥ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት፣ ከአራት ኪሎ እና ከእሪ በከንቱ የሚመጡ መንገዶች ፓርላማ መብራት ጋር፣ከሲግናል ወደ ካዛንቺስ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ ዝግ መሆኑ ታውቋል፡፡

በተጨማሪም ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ ስታዲዩም የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ ወይም ደንበል ሲቲ ሴንተር ፣ ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅድስ ዑራኤል ቤተ-ክርስቲያን መስቀለኛ ላይ ከላይና ከታች ፣ከተክለ ኃይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ኢሚግሬሽን የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል፣ ከተክለ ሃይማኖት ጎላ ሚካኤል የሚወስደው መንገድ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ፣ከጎፋ ፣ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር የሚወስደው አዲሱ መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከማለዳ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ ይሆናሉ፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ ከፖሊስ የተሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

ህብረተሰቡ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥመው ወይም የፖሊስ አገልግሎት ለማግኘት በአዲስ አበባ ፖሊስ የመረጃ ስልኮች 011-1 11-01-11 ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 መረጃ መስጠት እንደሚቻል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.