Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ከቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ከቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንትና በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሌሴጉን ኦባሳንጆ ጋር ተወያዩ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በአፍሪካ ልማት ባንክ ከምስራቅ አፍሪካ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አብዱል ካማራ(ዶ/ር) ጋርም በፅህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡

ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷”የግብርና ምርትን በመጨመር እንዲሁም የግብርና ምርቶች ዕሴት ጭማሪ ላይ እየተወሰዱ ያሉ አዳዲስ እርምጃዎችን በተመለከተ ክልላችን እና አገራችን ባካበቷቸው ተሞክሮዎች ላይ ተወያይተናል” ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.