Fana: At a Speed of Life!

ለብሔራዊ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፖሊሲ ሰነድ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፖሊሲ ሰነድ ላይ የባለድርሻ አካላት ግብዓት የማሰባሰቢያ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

ሰነዱ ከተቋሙ ምስረታ ማግስት የጀመረ የባለሙያዎች የሙያ ግብዓት እና ቅንጅት ታክሎበት የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ፖሊሲው ምቹ ስነ-ምህዳር የሚፈጥር፣ ወጣቶችን የሚያሳትፍ፣ የሕዝብን ጥያቄ የሚፈታ እና አሳታፊ መሆኑ ተመላክቷል።

የፖሊሲ ሰነዱ የሀገር በቀል ኢኮኖሚን ጨምሮ ሌሎች ሀገር በቀል አጀንዳዎችን ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀ እና አዲስ እድልን አሟጦ መጠቀም የሚያስች መሆኑ ተጠቁሟል።

ዘርፉ በደረሰበት እድገት ተግባራዊ ማድረግ ከዓለም ጋር ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት የግድ በመሆኑ መሰረተ ልማቶች በቀላሉ እንዲዘጋጁ አስቻይ ሁኔታዎችን መተግበር እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ማህበረሰቡ እንዲሳተፍ በማድረግ ዘርፉን መደገፍ አስፈላጊ መሆኑ በመድረኩ ተነስቷል፡፡

በፍሬህይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.