Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሚያደርገውን የልማት ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሚያደርገውን የልማት ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር  ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ህብረት የልማት ትብብር ሃላፊ  ስቴፋን ሎክ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

በወይይታቸው÷ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) መንግስት የመካከለኛ ዘመን የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድና የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያን በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ስቴፋን ሎክ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ረጅም ጊዜያትን ያስቆጠረ የልማት ትብብር ሲያደርግ እንደቆየ ማንሳታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የሰሜኑን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከስምምነት በመደረሱና ስምምነቱን ለማጽናት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ፍሬያማ መሆናቸውን ተከትሎ ህብረቱ ትብብሩን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚፈልግ አንስተዋል፡፡

ህብረቱ የልማት ትብብር ማዕቀፍ አዘጋጅቶ እያጠናቀቀ መሆኑን ያነሱት ሃላፊው÷ በህብረቱ ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ፍላጎት ጋር  እንዲጣጣሙ ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.