Fana: At a Speed of Life!

የማዕድን ሚኒስቴር ለወርቅ ኩባንያዎች ልዩ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስቴር ለወርቅ ኩባንያዎች ልዩ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ገለጸ፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) ከወርቅ አምራች ኩባንያዎች ጋር በ2016 በጀት አመት የምርት እቅድ ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ኩባንያዎቹ በሚቀጥለው አመት የተሻለ ምርት እንዲያመርቱ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግና ከወርቅ ኩባንያዎች የተሻለ ምርትና ገቢ እንደሚጠበቅም ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) ጠቅሰዋል፡፡

የኩባንያዎቹ የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው÷በስራ ላይ እያጋጠሟቸው ያሉትን ችግሮች በውይይቱ ላይ አንስተዋል፡፡

ከክልል እስከ ፌደራል ድጋፍ ከተደረገላቸው ያስቀመጡትን የወርቅ ምርት እቅድ ለማሳካት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል፡፡

ሚኒስቴሩ የኩባንያዎቹን ችግሮች ለመፍታት የጀመረውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥልም መገለጹን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ለ2016 በጀት አመት እቅድ መሳካትም በጋራ ለመስራት የሥራ ሀላፊዎቹ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.