Fana: At a Speed of Life!

የአርሶ አደር ይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ይፋዊ ርክክብ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው እለት 3 ሺህ 451ለሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደሮች የአርሶ አደር ይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ይፋዊ ርክክብ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

በርክክብ መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የይዞታ ማረጋገጫ ርክክብ ስነ-ስርዓቱ እየተካሄደ የሚገኘው በከተማዋ ስር ካሉ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ተመዝግበው ለተለዩ 3 ሺህ 451 አርሶ አደሮች ነው ተብሏል፡፡

አርሶ አደሮቹም ከለሚኩራ 1 ሺህ 446 ፣ ከቦሌ 819፣ ከአቃቂ ቃሊቲ 692፣ ከየካ 268፣ ከኮልፌ ቀራኒዮ 156 እንዲሁም ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 74 አርሶ አደሮች መሆናቸውን ከአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.