Fana: At a Speed of Life!

በፈረንሳይ የተቀሰቀሰው ግጭት እና ሁከት ተባብሶ መቀጠሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ ፖሊስ በአንድ ወጣት ላይ የፈፀመውን ግድያ ተከትሎ የተቀሰቀሰው ግጭት እና ሁከት ተባብሶ መቀጠሉ ተስምቷል፡፡

ግጭቱ አንድ የፖሊስ ኦፊሰር የአልጀሪያ ዜግነት ያለውን የ17 ዓመት ወጣት “ትራፊክ ጥሶ አልፏል” በሚል ተኩሶ መግደሉን ተከትሎ የተፈጠረ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

በዚህም በርካታ ሰላማዊ ሰልፈኞች በተለያዩ ከተሞች ሁከት እና ግጭት መፍጠራቸው የተሰማ ሲሆን፥ እስካሁን ከግጭቱ ጋር በተያያዘ 667 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በ17 ዓመቱ ታዳጊ ላይ የተፈፀመውን ግድያ አውግዘው÷ ፖሊስ በታዳጊው ላይ የወሰደው ምላሽ ያልተመጣጠነ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የፈረንሳይ ፖሊሶች ዘረኛ ናቸው በሚል የሚቀርበው ትችት ሀሰተኛ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ በተለይም አንዳንድ ፖለቲከኞች ክስተቱን ለማባባስ እየሞከሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በሀገሪቱ እስካሁን በተፈጠረው ሁከት 249 የፖሊስ አባላት ጉዳት እንደደረሰባቸው ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.