አትሌት ገንዘቤ በአንትሪም ኮስት ግማሽ ማራቶን እንደምትሳተፍ አስታወቀች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በሰሜናዊ አየርላንድ አንትሪም ኮስት በሚካሄደው ግማሽ ማራቶን እንደምትሳተፍ አረጋግጣለች፡፡
አትሌት ገንዘቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጿ ባሰፈረችው መልዕክት÷ ነሐሴ 27 በሚካሄደው የአንትሪም ኮስት ማራቶን እንደምሳተፍ ስገልፅ በከፍተኛ ደስታ ነው ብላለች፡፡
ከዚህ በፊት በአየርላንድ አንተሪም ኮስት ተሳትፋ እንደማታውቅም ነው የገለጸችው፡፡
አድናቂዎቿ በተጠቀሰው ቀን እና ቦታ ተገኝተው እንዲያበረታቷትም ጠይቃለች፡፡