Fana: At a Speed of Life!

ከ238 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሰኔ 16 እስከ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከ238 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በተጨማሪም የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 22 ግለሰቦች እና 11 ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተመልክቷል፡፡

የተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎችም÷ 169 ሚሊየን የገቢ እና ከ68 ሚሊየን ብር በላይ ደግሞ የወጪ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙት በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች መሆኑን የጉምሩክ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል÷ አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድኃኒት፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ ነው የተያዙት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.