Fana: At a Speed of Life!

በሐዋሳ ከ550 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐዋሳ ከተማ ከ550 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ (ረ/ፕ) ፕሮጀክቶቹን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡
ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች 16 መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ከእነዚህ መካከልም የሲዳማን ባሕል በሚያንጸባርቅ መልኩ የተገነባው የሐዋሳ መግቢያ በር አንዱ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም ወጪ ቆጣቢ ቤቶች፣ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ቢሮዎች፣ የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክቶች፣ በከተማው የተለያዩ ቦታዎች የተተከሉ ዘመናዊ ካሜራዎች ይገኙበታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.