Fana: At a Speed of Life!

የጂቡቲ የዲፕሎማሲ ልዑካን ቡድን ጉብኝት የሕዝቦችን ወንድማማችነት የሚያጠናክር ነው – አምባሳደር ብርቱካን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጂቡቲ የዲፕሎማሲ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ያደረገው ጉብኝት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን በማጠናከር ረገድ ሁኔታዎችን እንደሚቀይር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገለጹ፡፡

በትናንትናው ዕለት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በሸገር ከተማ አስተዳደር ለጂቡቲ የዲፕሎማሲ ልዑካን ቡድን አቀባበል አድርገዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ በንግግራቸው ይህ ታሪካዊ ጉብኝት በኢትዮጵያ እና በጂቡቲ መካከል ያለው ግንኙነት እየጎለበተ ስለመምጣቱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የሀገራቱን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በአቀባበሉ መርሐ-ግብር ላይ የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡

ከንቲባው በጂቡቲ እና በሸገር ከተማ አስተዳደር መካከል ግንኙነት መመሥረት እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.