Fana: At a Speed of Life!

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች የጤና ዐውደ ርዕይን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28 ቀን 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማቱ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን ሀገር አቀፍ የጤና ዐውደ ርዕይ ጎበኙ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር)÷ የጤና አገልግሎትን ዲጂታላይዝ ለማድረግና በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ለመደገፍ የሚደረገው ጥረት የጤናው ሴክተር እየጎለበተ መምጣቱን እንደሚያመላክት ተናግረዋል፡፡

ለአብነትም የቲቢ በሽታ መድኃኒት የሚወስዱ ታካሚዎችን በዲጂታል ዘዴ ለመከታተል የሚያስችል ሥርአት መዘርጋቱ የጤናውን ዘርፍ ስኬት ያሳያል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርም በሳኒቴሽንና በንጹህ  መጠጥ ውኃ አቅርቦት በርካታ ሥራዎችን በመስራት ለጤናው ዘርፍ ስኬታማነት አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.