Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ ለምክር ቤቱ የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ላይ ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት በ2015 በጀት ዓመት በመንግስት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የሚሰጡትን ምላሽና ማብራሪያ ያዳምጣል፡፡

ምክር ቤቱ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ጉባዔውን ነገ ያካሂዳል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌደራል መንግስት የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምክር ቤቱ በውሎው የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2016 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ የበጀት አዋጁን እንደሚያጸድቅ የሚጠበቅ መሆኑን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.