Fana: At a Speed of Life!

ሀገር በቀል የሕክምና ዕውቀትን ከዘመናዊው ጋር ለማስተሳሰር እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር በቀል የሕክምና ዕውቀትን ከዘመናዊ ሕክምና ጋር ለማስተሳሰር እየተሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ ገለጹ።

ሀገር በቀል የሕክምና ዕውቀት ለጤናው ዘርፍ ያለው አስተዋፅኦ እና የመድሐኒት ዘርፉ ያለፉት ዓመታት ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ አውደ- ጥናት በሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል።

የባሕል መድሐኒት÷ ከውጤታማነቱ ፣ ከደህንነቱና ከፈዋሽነቱ ጋር ተያይዞ ባሉ ጉዳዮች ከአርማወር ሃንሰን የምርምር ኢኒስቲትዩት ጋር በትብብር እየተሠራ መሆኑን ዶ/ር አየለ ተሾመ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያን የባሕል መድሐኒቶች በአግባቡ አውጥቶና አዘምኖ በጥቅም ላይ የማዋል ሥራ የሚመለከታቸው አካላት ድርሻ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በዘርፉ የተዘጋጁ ፖሊሲዎች ወደ ተግባር በመቀየር ረገ ድ፣ በቂ ጥናት አለመደረጉ፣ ቅንጅታዊ አሠራር ያለመኖሩን፣ የሚመደበው በጀት ዝቅተኛ መሆኑ የባሕላዊ ሕክምናው በዘመናዊ መንገድ እንዳያድግ ማነቆ መሆናቸው በአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች ተነስተዋል፡፡

የባሕላዊ ሕክምና ባለሙያዎችም የዘርፉን የሕክምና ዕውቀት ለትውልድ የማስተላለፍ ሂደቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀዛቀዘ መምጣቱን ጠቅሰዋል፡፡

ማኅበረሰቡ ለባሕላዊ ሕክምና ያለው አሉታዊ አመለካከት ሰዎች ጥበቡን ከቤተሰባቸው ለመውረስ ያላቸውን ተነሳሽነት ዝቅተኛ አድርጎታል ማታቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና አጋር ድርጅቶች እንዲሁም የባሕላዊ ሕክምና ማኅበራት ስትራቴጂዎችንና መመሪያዎችን በማዘጋጀት ዘርፉን የማዘመን ሥራ እንዲሠሩ ተጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.