Fana: At a Speed of Life!

የማህበረሰቡን ችግር በተገቢ ሁኔታ ለመቅረፍ  ግብርን በአግባቡ መሰብሰብ ያስፈልጋል – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር/ ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች መቅረፍ ሚቻለው ግብርን በአግባቡ መሰብሰብ ሲቻል ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር/ ኢ/ር) ገለጹ፡፡

የታክስ እና ጉምሩክ ሕግ ተገዥነትና የደረጃ “ሐ” የገቢ አሰባሰብ የንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በንቅናቄው መልዕክት ያስተላለፉት ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር/ ኢ/ር)  ÷በክልሉ ገቢ ለመሰብሰብ የታቀደውን ዕቅድ ለማሳካት ባለድርሻ አካላት ያበረከቱት አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ የተከናወነው የገቢ መሠረትን የማስፋት እና የግብርና የታክስ አሰባሰብ ስርዓት በቀጣይ አጠናክሮ ለማስቀጠል ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ ገቢን በፍትሃዊ መሰብሰብ ሲቻል ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ÷ከግብርና ታክስ አሰባሰብ ስርዓት ባሻገርም የግብር ከፋዩን ቅሬታ መፍታት ይገባል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.