Fana: At a Speed of Life!

አርባ ምንጭ ከተማ ወደ ታችኛው ሊግ ወርዷል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አርባ ምንጭ ከተማ ወደ ታችኛው ሊግ የወረደ ሶስተኛው ቡድን ሆኗል፡፡

አርባ ምንጭ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት ያደረጉት ጨዋታ በአንድ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም አርባ ምንጭ ከተማ በ34 ነጥብ ወደ ታችኛው ዲቪዚዮን የወረደ ሲሆን÷ በአንጻሩ ወልቂጤ ከነማ ከመውረድ ተርፏል፡፡

ወልቂጤ ከነማ ከአዳማ ከነማ ጋር ያደረገው ጨዋታ በተመሳሳይ አንድ አቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን÷በዚህም 35 ነጥብ በመያዝ ወደታችኛው ዲቪዚዮን ከውረድ ሊተርፍ ችሏል፡፡

አርባ ምንጭ ከተማ በአጥቂዎቹ ኤሪክ ካፓይቶ፣ አህመድ ሁሴን፣ መላኩ ኤሊያስ እና ቡጣቃ ሻመና በርካታ የግብ እድሎችን ቢያገኝም በሀዋሳ ከተማው በረኛ አላዛር ማርቆስ ከሽፈዋል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ መቻል ለገጣፎ ለገዳዲን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.