Fana: At a Speed of Life!

በክልሎች ሲተገበር የቆየው የግሪን ፒፕል ኢነርጂ ፕሮጀክት ውጤታማ መሆኑ ተመለከተ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ፣ ሲዳማ እና ከፊል ኦሮሚያ ክልሎች ሶላር ኢነርጂን በመጠቀም ለሦሥት ዓመታት በሙከራ ደረጃ ሲተገበሩ የነበሩ ቴክኖሎጂዎች ውጤታማ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

ፕሮጀክቶቹ ውጤታማ መሆናቸውን ተከትሎም ለማኅበራት ተላልፈው መሰጠታቸውን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሡልጣን ወሊ (ዶ/ር ኢ/ር)÷ ለማኅበራት ከተላለፉት መካከል የአትክልት ማቀዝቀዣ፣ የሚኒ ሀይድሮ ፓወር ጥገና እና የሶላር ፓምፕ ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል፡፡

ዛሬ ለማኅበራት የተላለፉት ቴክኖሎጂዎች ፕሮጀክት ወጪ በጀርመን ተራድኦ ድርጅት (ጂ አይ ዜድ) ኢትዮጵያ መሸፈኑ እና ሥራው ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በትብብር መከናወኑ ተጠቁሟል፡፡

የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ከተጀመረ ስድስት ዓመታት ማስቆጠሩ ተመላክቷል፡፡

በዚህ ፕሮግራምም ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዲሆን÷ ከዓለም ባንክ፣ ከጀርመን ተራድኦ ድርጅት (ጂ አይ ዜድ) እና ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ አይ ዲ) ጋር በመተባበር እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.